በ10 ዓመት ኮደር፣ በ19 ዓመት የሶፍትዌር አበልጻጊ፡ ታዳጊዋ የቴክኖሎጂ ንግድ ስራ ፈጣሪ ቤተልሄም ደሴን እንተዋወቅ

(በቤተልሄም ደሴ መልካም ፈቃድ የተጻፈ)

(በቤተልሄም ደሴ መልካም ፈቃድ የተጻፈ)

የቤተልሄም 9ኛ ዓመት የልደት በዓል ላይ አባቷ ስራ ስለነበረባቸው ልደቷን ሊያከብሩላት ስላልቻሉ ነበር የቴክኖሎጂ ንግድ ስራ ፈጣሪ በመሆን የልደቷን ወጪ በራሷ ለመሸፈን የወሰነችው። 

የስራ መስኩ ገንዘብ የማመንጨት አቅም ስለሳባት ቤተልሄም በትውልድ ከተማዋ ሐረር፣ ኢትዮጵያ ውስጥ በአካባቢዋ በሚገኝ የኮምፒዩተር ጥገና እና የቪድዮ ኤዲቲንግ መደብሮች አካባቢ በመዋል ሙያውን ማጥናት ጀመረች። የጉግል ፍለጋዎችና በአካባቢዋ ካሉ ኮሌጆች የምትዋሳቸው መጽሐፍት እውቀቷን እንድታሰፋ አግዘዋታል።

ከጥቂት ጊዜ በኋላም ቤተልሄም ከትምህርት ሰዓት በኋላ ከምትሰራው ቴክኖሎጂ ነክ ስራዋ ገንዘብ ማግኘት የጀመረች ሲሆን ቪድዮ ኤዲቲንግና የሞባይል ስልክ ሶፍትዌር መጫን የስራዋ አካል ነበር። “ያን ገንዘብ ለማግኘት መቻሌ ከፍተኛ የራስ መተማመንና ራስን የመቻል ፍላጎትን አሳደረብኝ። ያ ስሜትም ለረጅም  ጊዜ እንዲቆይ እፈልግ ነበር” በማለት በስራው መስክ ላይ የመጀመሪያ ፍላጎት ያሳደረባትን ሁኔታ ታስረዳለች። 

ቤተልሄም ተፈጥሯዊና እጅግ አስደናቂ የሆነ የቴክኖሎጂ እና ኮዲንግ ችሎታ እንዳላት አሳይታለች። ችሎታዎቿ ባደጉ ቁጥር ዝናዋም አብሮ  አደገ። የሃገር ውስጥ የዜና ምንጮች የቤተልሄምን ታሪክ መዘገብ ጀመሩ። የ10 ዓመት ልጅ እያለች ነበር የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ እርሷና ቤተሰቦቿ ወደ ርዕሰ መዲናዋ አዲስ አበባ መጥተው እንዲኖሩ ጋበዧቸው። መንግስት የቤተልሄምን የትምህርት ወጪ በመሸፈን ሚስጥራዊ የሶፍትዌር ማበልጸጊያ ፕሮጄክቶች ላይ እንድትሰራ አደረገ።

ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ቤተልሄም ክህሎቶቿን ጥቅም ላይ በመዋል ስራ ተጠምዳ ቆይታለች፤ አራት የሶፍትዌር ፕሮግራሞችን አበልጽጋ የኮፒራይት የተቀበለች ሲሆን ከእዚህም ውስጥ ገና 10 ክፍል እያለች የፈጠረችው ዲጂታል ላይብረሪ አንዱ ነው። ፕሮግራሙ ውስን የኢንተርኔት አገልግሎት የሚያገኙ ት/ቤቶች ተማሪዎቻቸው ለመማር የሚያስፈልጋቸውን መረጃዎች እንዲያገኙ የሚያስችል ነው። ቤተልሄም መንግስት የወንዞችን አቀማመጥ በመለየት የመስኖ ስርዓቶችን ለመከታተል የሚያስቸለው መተግበሪያም ፈጥራለች። ስማርት ስልክ ያለው ማንኛውም የግብርና ባለሙያ ለመተግበሪያው አስተዋጽኦ ማድረግ ይችላል። 

አሁን የ19 ዓመት ወጣት የሆነችው ቤተልሄም ቴክኖሎጂ የልደት በዓላትን ወጪ ለመሸፈነ ከሚያስገኘው ገንዘብ እጅግ የበለጠ አገልግሎት የመስጠት አቅም እንዳለው ተገንዝባለች። “ለአፍሪካ ቀጣዩ ታላቅ ነገር ቴክኖሎጂ ነው ብዬ አምናለሁ” ትላለች። “አፍሪካ ውስጥ ያለን ታላቅ ነገር ወጣቱ ትውልድ ነው። ስለዚህ፣ ወጣቱን ትውልድ በቴክኖሎጂ ካሰለጠንነው፣ ረዥም አድሜ ያለው ነገር ለመገንባት እንችላለን።”

ቤተልሄም ቀጣዩ የኢትዮጵያ ትውልድ እነዚህን አጋጣሚዎች ለመጠቀም የሚያስፈልገውን ክህሎት ለማስጨበጥ ትፈልጋለች። ኢትዮጵያ ውስጥ የመጀመሪያ የሆነው አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) የምርምር መአከል በሆነው iCog Labs ውስጥ በፕሮጄክት ስራ አስኪያጅነት የምትሰራው ቤተልሄም ሴት ልጆች በመስኩ ያላቸውን ተሳትፎ ለመጨመር የተለያዩ ፕሮጄክቶች ላይ ትሰራለች። Anyone Can Code በሚለው የ iCog ፕሮግራም አማካይነት ቤተልሄም በመላ ሃገሪቱ በመዘዋወር ከ 8 እስከ 18 ዓመት እድሜ  ያላቸው ልጆች ቴክኖሎጂያዊ ክህሎቶችን እንዲማሩ ታግዛለች። ከት/ቤት በኋላ በሚሰጡ ፕሮግራሞችና በክረምት ካምፖች አማካይነት ቤተልሄምና የስራ አጋሮቿ የኮዲንግ እና ሮቦቲክስ መሰረታዊ እውቀቶችን ለተማሪዎች ያስተምራሉ። 

“እነዚህን የኮዲንግ ወይም ሮቦቲክስ ክህሎቶች ሲማሩ በታላቅ ደስታ ነው” ትላለች ቤተልሄም። “የሚያሳዝነው ግን እነርሱ ቢፈልጉም እንኳን የ2ኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ተግባራዊ ለማድረግ ዐቅም አይኖራቸውም።” እንደ ቤተልሄም ገለጻ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ሴት ልጆች በ1ኛና 2ኛ ደረጃ ት/ቤት እያሉ በ STEM የትምህርት ዓይነቶች የላቀ ውጤት ቢኖራቸውም ከወላጆቻቸው ማበረታቻ ባለማግኘታቸው ምክንያት እነዚህን መስኮች በሙያ ደረጃ ይዘው አይቀጥሉም። 

“ወላጆችሽአንቺአድገሽምንእንደምትሆኚየሚጠብቁትነገርአለ፤ጎበዝተማሪከሆንሽወደፊትመሆንያለብሽዶክተርእንጂኢንጂነርወይምበኮምፒዩተርሳይንስመስክውስጥአትሰማሪም” ትላለች። “በ STEM ውስጥተሰማርታስኬታማየሆነችሴትከዚህበፊትአይተውአያውቁም።” በዝርዝሯውስጥያሉትቴክኖሎጂያዊፈጠራዎችያለማቋረጥእያደጉበመሆናቸውቤተልሄምይህንትርክትለመየቀየርዕቅድአላት።

This piece is available in Arabic, English, French and Spanish.

 
 

Through Assembly, Malala Fund is helping girls around the world share their stories. Subscribe to receive our newsletter and learn about the next generation of leaders.


 

About the author

Tess Thomas is editor of Assembly, a digital publication and newsletter from Malala Fund. She loves books, cats and french fries.